yooyaapress.com
info @yooyaapress.com

በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ

Ethiopian Muslim logo
በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ ከኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገው በዉይይቱ ላይ በሙስሊም ተወካዮች ከተነሱት ነጥቦች መካከል፦
  1. በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች የመስጂድ መሬትን በህጋዊ መንገድ የማግኘትና የመሥራት እንዲሁም ለተሠሩት መስጂዶች ካርታና የማስፋፊያ መሬት የማግኘት ሁኔታ ላይ በርካታ ችግሮች እንዳሉ በዝርዝር ተብራርተዋል።
  2. የሸገር ከተማ አሰተዳደር ከፕላን ዉጭ ተሠርተዋል ያላቸውን መስጂዶች ለማፍረስ ሲነሳ የሚመለከተውን የእስልምና ጉዳዮች አካላትን እንዳለወያየ፥ እንዲሁም በጉዳዩላይ እንወያይ በሚል በተደጋጋሚ ጊዜ የቀረበውን ጥያቄ ተቀብሎ ለማወያየት አለመሞከሩ ተገቢ አለመሆኑ በቅሬታ መልክ ቀርቧል።
  3.  ሕዝበ ሙስሊሙ የሸገር ከተማ መስጂድ ፈረሳ ጋር በተያየዘ በተፈጠሩት ሁኔታዎች እጅጉን መጎዳቱንና ማዘኑን በማብራራት ተገቢውን #ካሳና #የሞራል ህክምና እንደሚያስፈልገው ተጠቅሷል፡
  4.  የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም ሆነ ሕዝበ ሙስሊሙ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ከተሞችን ለማዘመን የሚደረገውን እቅድን፥ ልማትንም ሆነ አድገትን የሚደገፍው እንጂ የሚቃወመው እንዳልሆነ ሆኖም እቅዱ በቂ የእምነት ተቋማትን ለአማኞች ማቅረብንና ሰው ተኮር መሆን እንደሚገባው ተብራርቷል።
  5. በሸገር ከተማ አስተዳደር ዉስጥ ያለ ፕላንና ሕጋዊነት ተሠርተዋል በሚል የፈረሱት 22 (ሃያ ሁለት) መስጊዶች መሆናቸውን በመጥቀስ ለሕዝበ ሙስሊሙ የመስጊጅ ጥያቄዎች በሙሉ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚገባ ተነስቷል
  6.  ቀደም ብሎ በጉዳዩ ላይ ከጅምሩ በመነጋገር መፍታት እየተቻለ እስከ ትናንትናው እለት ድረስ መሰል ዉይይት ሳይደረግ መስጂዶችን ወደ ማፍረስ በመግባቱ በመንግስትና በሕዝብ መካከል ቅሬታ ፈጥሮ ጉዳዩ እስከ ነፍስ መጥፋት ማምራቱ እጅግ የሚያሳዝን መሆኑን፤
  7. የጸጥታ አካላት ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ በቀጥታ በመተኮስ ሙስሊሞችን መግደላቸውና ማቁሰላቸው ተገቢ አለመሆኑን እንዲሁም ንጹሃን ላይ በመተኮስ የገደሉና ያቆሰሉ አካለት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተጠይቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *